በሊቢያ የነበሩ 117 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ

)በሊቢያ የነበሩ 117 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ።

በዛሬው እለት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ኢትዮጵያውያን በሊቢያ በአሰቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ስደተኞቹ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት በግብጽ የኢፌዴሪ ኤምባሲ እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ጥረት መሆኑም ተገልጿል።

በሊቢያ የነበሩት 117 ኢትዮጵያውኑ በተዘጋጀላቸው ልዩ በረራ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ኤምባሲው ለተመላሽ ስደተኞች አስፈላጊ የሆኑ የጉዞ ሰነዶችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር ተባብሮ በማሟላት የተቀሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሊቢያ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝት ገልጿል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *