ተመድ እና የአፍሪካ ህብረት በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እየመጣ ያለውን ለውጥ አደነቁ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እየመጣ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት የጋራ ግብረ ሀይል በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 73ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን 15ኛ መደበኛ ስብሰባቸውን አድርገዋል።

በስብሰባቸውም በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እየመጣ ያለው ለውጥ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፥ ለውጡንም አድንቀዋል።

የጋራ ገብረ ሀይሉ በተለይም የቀጠናው ሀገራት መሪዎች በመካከላቸው ያለውን አለመግባባቶች ለመፍታት ያሳዩት ከፍተኛ የአመራር ብቃት ለቀጠናው ሰላም ትልቁን ሚና ተጫውቷል ሲል የጋራ ገብረሀይሉ አድናቆቱን ገልጿል።

ይህ ተግባርም ለሌሎች ከድንበር ጋር ተያይዞ ለሚወዛገቡ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን መሆኑንም የጋራ ግብረ ሀይሉ በስብሰባው አንስቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እየመጣው ያለው ለውጥ ቀጣይነት እነዲኖረው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም የጋራ ገብረ ሀይሉ አስታውቋል።

የአፍሪካ ህብረትም በምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የተውጣጣ አዲስ ቡድን እንዲቋቋምም ጥያቄ ማቅረቡን የተመቅ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *