አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀረቡ

በኤርትራ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ አቅርበዋል።

በወቅቱ አምባሳደር ሬድዋን ባደርጉት ንግግር፥ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከፍ ባለበት ዘመን በኤርትራ እንዲሰሩ መመደባቸው ያስደሰታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በኤርትራ ቆይታቸው የሁለቱን አገሮች ዲፕሎማሲያዊና ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ከፍ ለማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ በበኩላቸው መንግስት የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ከፍ ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት የመንግስት ድጋፍ የማይለያቸው መሆኑን ኦስማን ስልህ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *