አርቲስትና አክቲቪት ታማኝ በየነ ነሃሴ 26 ወደ ሃገሩ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል

Qeerroo Tube

ነሀሴ 22፣2010

ከ20 አመታት በላይ በስደት የኖረው አርቲትስት እና አክቲቪት  ታማኝ በየነ በመጪው ነሃሴ 26  ጠዋት  ወደ ሃገሩ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የታማኝ በየነ የአቀባበል ብሔራዊ ኮሚቴ እንደገለፀው ነሃሴ 27 ከቀኑ በ10 ሰአት በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው ዝግጅት ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የታማኝ አድናቂዎች እና ወዳጆች ከክፍያ ነፃ የሆነ የመግቢያ ትኬት በአዲስ አበባ ከተማ በ 10ሩም ክፍለ ከተሞች ፅህፈት ቤቶች እንደሚያገኙ  ኮሚቴው ገልጿል፡፡

አርቲስት ታማኝ በየነን ለመቀበል የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ አባላትም በአቀባበል ስነ ስርአቱ ላይ ስለሚኖረው ዝርዝር መርሃ ግብር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ታማኝ በየነ ለአመታት ፍቅርን እና አንድነትን ሲሰብክ የቆየ እና በማይመች ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ሃገሩን የሚያስቀድም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነው   ያሉት ደግሞ  ጓደኞቹ እና የሙያ አጋሮቹ ናቸው፡፡

ሪፖርተር:-አዲስዓለም ተሾመ

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *