ኤርትራ ተጨማሪ ወደብ ልትገነባ መሆኑን ተገለጸ

ነሀሴ18፣2010

ኤርትራ በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማስተናገድ እንዲያስችላት ተጨማሪ ወደብ ልትገነባ መሆኑን ብሉምበርግ አስነብቧል።ERITREA-ECONOMY-POLITICS-PORT

 

በኤርትራ በኢነርጂና ማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ዳይሬክተር አለም ክብረኣብ ኤርትራ በቀይ ባህር ላይ የምትገነባው ወደብ በተለይ በኢትዮጵያ የሚመረተውን የፖታሽ ማዕድን ወደ ሶማሊያ፣ ጁቡቲ እና ሶማሌላንድ ማጓጓዝ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ወደቡ በሚለማበት አከባቢ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን የፖታሽ ማዕድን ክምችት መኖሩን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የወደቡ ግንባታ በአምስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ወደቡ የሁለቱን አገራት የፖታሽ ማዕድን ለማጓጓዝ አዋጭ ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ከፈረሙ በኋላ በቀጠናው በጋራ የመልማት አዝማሚያ እያደገ መሆኑን የብሉምበርግ ዘገባ አመልክቷል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *