ከ9 ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

ከዘጠኝ ሀገራት የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ።

የኢንዱስትሪ ፓርኩን ከዘጠኙ የውጭ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተውጣጡ 32 ተወካዮች ናቸው የጎበኙት።

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ፥ ለጎብኚዎቹ ስለ አጠቃላይ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኢንዱስትሪ ፓርኩ ስለ ፈጠረው የስራ እድል፣ የወጪ ንግድ መር ስለመሆኑ እንዲሁም የኢትዮጵያን ወደ ኢንዱስትሩ ሽግግር ያረጋግጣል ተብው ከሚጠበቁ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከማብራሪያው በመቀጠልም ፓርኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች፤ በተለየም የውሃ ማከሚያ ተቋሙ እና አንድ የተመረጠ ፋብሪካን ገብኝተዋል።

ከነዚህ መካከልም ተወካዮቹ በፓርኩ የሚገኘውን እና የታይዋኑን ኤቨረስት የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ማምረቻ ጎብኝተዋል፡፡

በፋብሪካው ባደረጉት ጉብኝትና በተመለከቱት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን በዚህ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየትም ኢትዮጵያ በትክክለኛ የዕድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ መታዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ የሚገኘው የታይዋኑ ኤቨረስት ፋብሪካ ለ1 ሺህ 500 ሰራተኞች እንዳሉትም ተገልጿ፡፡

ከጎብኚዎቹ መካከልም የጀርመኑ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ኮንስታንቲን ግራንድ በሐዋሳ ኢንዱስትርያልፓርክ ባዩት ነገር መገረማቸውን ተናግረዋል፡፡

ተወካዩ ኢትዮጵያ ወደ ማምረቻው ዘርፍ እያደረገች ያለው ሽግግር በጥሩ መስመር ላይ መሆኑን መታዘብ መቻላቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

በፓርኩ የስራ ዕድል ከመፍጠር አንጻርም ትልቅ ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡
ፓርቲያቸው ዕድገት ማስመዝገብ በሚቻልበት አግባብ ከኢህአዴግ በጋራ በእንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

የሩዋንዳው አርፒኤፍ ፓርቲ ተወካይ ሚስተር ቲቶ በበኩላቸው በጉብኝቱ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ለአፍሪካ ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ የስራ ዕድል ከመፍጠርም ሆነ ምርቶቹን ወደ ውጭው ከመላክ አንጻር አመርቂ ስራ መሰራቱንም በጉብኝታቸው ወቅት መታዘባቸውን አንስተዋል፡፡

የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በአህጉር ደረጃ ያለውን የገበያ ክፍተት መሸፈን የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው ሀገራቸው ከፓርኩ ልምድ መቅሰም እንደምትችል ገልጸዋል፡፡

የየፓርቲው ተወካዮች የፓርኩን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ከኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ውይይት እንደሚያካሄዱም ይጠበቃል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ በትናንትናው እለት በተጀመረው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በእንግድነት ተጋብዘው የመጡ ናቸው።

የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮቹ የጅብቲው ገዥ ፓርቲ አር ፒፒ፣ የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ሲፒሲ፣ የኬንያው ገዥው ፓርቲ ጁብሊ፣ ሩዋንዳው ገዥ ፓርቲ አርፒኤፍ፣ የጀርመን የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ፣ የሱዳን፣ ታንዛኒያ የደቡብ አፍሪካ እና የቬትናም ፖለቲካ ፓርቲ ናቸው።

በባህሩ ይድነቃቸው

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *