የቪዬትናም ፕሬዝዳንት ቻን ዳይ ኳንግ አዲስ አበባ ገቡ

Qeerroo Tube

ነሃሴ 17/2010

የቪዬትናም ፕሬዝዳንት ቻን ዳይ ኳንግ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

Screen Shot 2018-08-24 at 7.39.25 AM

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በፕሬዝዳንት ደረጃ የቪዬትናም መሪ ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ቻን ዳይ ኳንግ የመጀመሪያ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ቻን ዳይ ኳንግ በጉብኝታቸው ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ጋር ይወያያሉ።

ፕሬዝዳንት ቻን ዳይ ኳንግ በሚኖራቸው ቆይታ በሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ትብብር ስምምነት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቶች መካከል ቋሚ የፖለቲካ ምክክር የማካሄድ እንዲሁም የዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፓስፖርት ተጠቃሚዎችን ያለ ተጨማሪ ሁኔታ ማስተናገድ የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶች ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቬትናም የልዑካን ቡድን የቢዝነስ ማህበረሰብ አባላት ከሀገራችን የግሉ ዘርፍ የቢዝነስ ማህበረሰብ አባላት ጋር እንደሚወያዩና ቋሚ ግንኙነቶችን ይመሰረታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *