የአዲስ ዓመት ስጦታ ለእናት ሃገሬ” ዝግጅት ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

qeerroo_tube_new_year gift

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጳጉሜ 01/2010

የአዲስ አበባ መስተዳድር “የአዲስ ዓመት ስጦታ ለእናት ሃገሬ” በሚል ርዕስ ከነሃሴ 28/2010 እስከ ጳጉሜ 01/2010 ድረስ ለተቸገሩ ሰዎች ያዘጋጀው የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በጥሬ ገንዘብ ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱ ተገልጿል፡፡

ከጥሬ ገንዘቡም በተጨማሩ በዓይነት የተለያዩ ቁሳቁሶችና የደም ልገሳ መካሄዱንም አቶ ነስረዲን ሙሃሙድ የበጎ ፍቃድ ዝግጅቱ አስተባባሪና የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

በደም ልገሳ በኩል 500 ዩኒት ደም መገኘቱንና በትምህርት መርጃ መሳሪያዎችም ረገድ ደብተር፤ እስክሪቢቶና ሌሎችንም ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ በአይነት መለገሱን ገልጸዋል፡፡

የአዋቂና የልጆች አልባትም የተለገሱ ሲሆን እስካሁንም ከ600 ማዳበሪያዎች በላይ ከህብረተሰቡ መሰደጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከ190 ማዳበሪያዎች በላይ የአዋቂና የልጆች እንዲሁም የሴቶች እና የወንዶች ጫማዎችም ተለግሰዋል፡፡

ሶፍት ሳሙናና መሰል የንጽህና መጠበቂያ ቀሳቁሶችም በቁጥር ከ3800 በላይ እንደተሰጡ ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶነስረዲን ሙሃሙድ ገለጻ ዘይት፤ ዱቄት፤ ስኳርና ሌሎች መሰል የምግብ አይነቶች ደግሞ 400 ኪሎ ግራም ያህል ተለግሰዋል፡፡

ወንበሮች፤ የህጻናት መጫወቻዎችና ሌሎች መሰል የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች በቁጥር ከ1000 በላይ እንደተለገሱ ነው የተናገሩት፡፡

ፎቶ – በናትናኤል ጸጋዬ

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *