የኢሬቻ በዓል አንድነታችንንና ሰላማችንን ለማወክ ለሚፈልጉት ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል– አቶ ለማ መገርሳ

“የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አንድነታችንንና ሰላማችንን ለማወክ ለሚፈልጉ ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል” አሉሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ።

ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ በቢሾፍቱ ከተማ በትናንትናው እለት የተከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ “በዓሉ ፍጹም ሰላሚ እንደነበረ ገልፀዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው መላው ህብረተሰብ ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ  ምስጋና አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ ልዩ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ለአባ ገዳዎች ምክር ቤት፣ ለክልሉ ወጣቶች (ፎሌ)፣ ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፣ ለፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም ለቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቀርበዋል።

ዘንድሮ በዓሉ ሰላማዊ ከመሆኑም ባሻገር ከክልሎች በስፍራው የተገኙና በበዓሉ ላይ የታደሙ ብሄር ብሄረሰቦች ልዩ ድምቀት እንደሰጡት ነው የገለጹት።

ይህም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ከቆሙ ሁሉንም ነገር ማሳካት እንደሚችሉ ማሳያ ሆኖ ማለፉን ጠቁመዋል።

“በዓሉ ያለፈው ሊከፋፍሉን ለሚፈልጉ፣ ትልቅ መልዕክት በማስተላለፍ  ነው” በማለት ነው ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ በአጽንኦት የገለጹት።

“በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ብቻ ተከትሎ እንዲከበር ወጣቶች ላደረጉት አሰተዋጽኦ ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ መስቀል ባለፈ በመጀመሪያ እሁድ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሀይቅ እንደሚከበር ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

 

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *