የኢትዮጵያ አየር ሃይል በአልሸባብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

qeerroo_tube_ethiopian_airstrike

የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን ነው በአሸባሪው ቡድን ላይ ጥቃን የፈጸመው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳስታወቀው ሰሞኑን የተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን ከደቡብ ምስራቅ ዕዝ እግረኛ ሰራዊት ጋር የጋራ ቅንጅት በመፍጠር በአሸባሪ ቡድኑ ላይ በወሰደው የአየር ሃይል ጥቃት ዘመቻ ያስመዘገበው ድል አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡

የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ይልማ መርዳሳ በተካሄደው ዘመቻ  በአልሸባብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቁሳዊና ሞራላዊ ውድመት እንደደረሰበት ተናግረዋል፡፡

አየር ሃይሉ የአገሪቱን የአየር ክልል ከመቼውም ጊዜ በላቀ ቁርጠኝነትና የወትሮ ዝግጁነት ደረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ ከመጠበቅ ባሻገር ለምድር ሃይሉ ጠንካራ ድጋፍ በመስጠት በአገሪቱ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ወረራና የሽብር ድርጊት በአጭር ጊዜ ለመመከት የሚችል ጠንካራ ተቋም መሆኑን ብ/ጄ ይልማ አስታውቀዋል..

የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ይልማ መርዳሳ ለዚህ ዘመቻ ስኬት ድርሻቸውን ላበረከቱ የአየር ሃይል ሰራዊት አባላት በተለይም ይህንን ታላቅ ግዳጅ ለተወጡ ለተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮንና ለምድቡ የሰራዊት አባላት ምስጋና አቅርበዋል..

 

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *