የ10 አመት ብሄራዊ የደን ልማት ፕሮግራም ይፋ ሆነ

የ10 አመት ብሄራዊ የደን ልማት ፕሮግራም በዛሬው እለት ይፋ ሆነ።

የአካባቢ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር ፕሮግራሙን በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ይፋ አድርጓል።

ለ10 አመት የሚተገበረው የደን ልማት ፕሮግራም በሃገሪቱ ለ600 ሺህ ዜጎች በደን ልማትና ተያያዥ ዘርፎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

እድገትን ከአረንጓዴ ልማት ጋር ማጣጣም እንደሚገባ ፕሮግራሙ ይፋ በሆነበት ወቅት ተገልጿል።

የደን ሃብትን በአግባቡ መንከባከብ በፈረንጆቹ 2030 ለመድረስ ለታሰበው የዘላቂ ልማት ግቦች መሳካት አጋዥ መሆኑም ነው በስነ ስርዓቱ ወቅት የተገለጸው።

ፕሮግራሙ የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከኢትዮጵያ፣ ከስዊድን እና ኖርዌይ መንግስታት ጋር በጋራ የሚያከናወን መሆኑን፥ ከመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *