ደቡብ አፍሪካ በድጋሚ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ውስጥ ገባች

ነሃሴ 29/2010

ደቡብ አፍሪካ ከፈረንጆቹ 2009 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ውስጥ መግባቷ ተነግሯል፡፡

በግብርና፤ ትራንስፖርት እና ንግድ ዘርፎች ውጤታ አለመሆናቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት በ0.7 ከመቶ መቀነሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ይህ መረጃ ይፋ ከተደረገ በኋላ የሃገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ራንድ የመግዛት አቅሙ በ2 ከመቶ ሲቀንስ የመንግስት ቦንድ ሽያጭ ዋጋም መውረዱ ተነግሯል፡፡

በመጨረሻው የሩብ አመትም የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት እድገትም ከ0.6 ከመቶ በታች እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

በተለይም ደግሞ የግብርና ዘርፉ ምርታማነት በ29.2 ከመቶ መቀነሱ ለምጣኔ ሃብቱ ውድቀት አስተዋዕኦ አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ሮይተርስ

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *