ጀነራል ሰዓረ መኮንን ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ

ነሀሴ18፣2010

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ክሪስ ስሚዝ ከመሩት ቡድን ጋር በቀጠናዊ ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

በውይይት መድረኩ ኢትዮጵያ በቀጠናው እያበረከተች ያለውን የፀጥታ ማስፈን ሚና አጠናክራ መቀጠሏን የጠቆሙት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጀነራል ሰዓረ መኮንን በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በደቡብ ሱዳን በዳርፉር እና በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ግዳጃቸውን በሚገባ እየተወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የቀጠናውን ሰላም ለማደፍረስ በጎረቤት አገር ሶማሊያ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው አልሸባብም በወታደራዊ ቁመናው እየተዳከመ መምጣቱንም ጀነራል ሰዓረ ጠቁመዋል፡፡

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፅሕፈት ቤት በተደረገው ውይይት ላይ በተለይም ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እያደረገች ያለውን አስተዋፅኦ አሜሪካ የምታደንቅ መሆኗን የአሜሪካ ኮንግረስ አባልና የልዑኩ መሪ ክሪስ ስሚዝ ተናግረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ፀጥታን በማስፈን በቀጠናው እያበረከተች ላለው አስተዋፅኦ ምሥጋናቸውን በማቅረብ አገራቸው ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአገር ውስጥና የውጭ ሥልጠና ድጋፍ እንደምታደርግም ክሪስ ስሚዝ ተናግረዋል፡፡

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *