ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሰዓታት በኋላ በፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ አውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ ይካሄዳል።

በውይይቱ ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ወደ ፍራንክፈርት ከተማ የመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ይጠበቃል።

በፍራንክፈርት ኮሜርስ አሬና በሚደረገው በዚህ ውይይት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎች እንደሚቀርቡም ነው የሚጠበቀው።

ከውይይቱ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የክብር ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሏል።

የመጀመሪያ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ ከትናንት በስቲያ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅት ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላቀረቡላቸው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ፈቃደኝነታቸውን ገልጸውላቸዋል።

በትናንትናው እለትም ከጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *