ጨፌ ኦሮሚያ አዲስ አፈ ጉባዔን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ።

ጨፌው በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው ወይዘሮ ሎሚ በዶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ በማድረግ መርጧል።

በዚህም መሰረት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ በነበሩት በአቶ እሸቱ ደሴ ምትክ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አፈ ጉባዔ በመሆን ተመርጠዋል።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ እሸቱ ደሴ ተደራራቢ የስራ ሀላፊነት ስላለባቸው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል።

አቶ እሸቱ ለነበራቸው ቁርጠኛ አመራር እና ተሳትፎም በክልሉ መንግስት እና በጨፌው ስም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

በተጨማሪም ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችንም አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1.ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊ

2.ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ዘርፍ ሀላፊ

3. አቶ አህመድ ቱሳ፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሀላፊ

4. አቶ አሰግድ ጌታቸው፦ የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊ

5. አቶ ዳባ ደበሌ፦ የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ

6. ዶክተር ኢንጂነር ፍቃዱ ፉፋ፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሀላፊ

7. አቶ ሙላቱ ጽጌ፦ የንግድ ቢሮ ሀላፊ

8. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ፦ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ሀላፊ

9. አቶ ገረመው ሁሉቃ፦ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

10. ወይዘሮ ሙና አህመድ፦ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ

11. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ

12. አቶ ጥላሁን ወርቁ፦ የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ

13. ወይዘሮ ፈቲያ መሃመድ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

14. አቶ ኤባ ገርባ፦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ

15. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

16. አቶ ተሾመ ግርማ ፦ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

በተጨማሪም ጨፌው በዛሬ ውሎው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦ ቢ ኤን) ዋና ዳይሬክተር እና የቦርድ አባላት ሹመትን አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦
 
1. ጋዜጠኛ መሃመድ አደሞ፦ የኦ ቢ ኤን ዋና ዳይሬክተር
 
2. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ ሰብሳቢ
 
3. ወይዘሮ ሌሊሴ ነሜ፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል
 
4. ዶክተር ደረጄ ገረፋ፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል
 
5. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል
 
6. ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ – የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል
 
7. ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል
 
8. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የኦ ቢ ኤን የቦርድ አባል በመሆን ተሾመዋል።
 
እንዲሁም ጨፌው 98 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እና 6 የወረዳ ፍርድ ቤት በድምሩ የ104 ዳኞችን ሹመትም ያፀደቀ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ሴቶች ናቸው።
 
በሰርካለም ጌታቸው
banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *