ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገቡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጁባ ሲደርሱም የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር እና ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናት በጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑት ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው።

በጁባ ጃን ጋራንግ አደባባይ በሚካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተፋላሚ ኃይሎች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኬንያ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ንግግር እንደሚያደርጉ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *