ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ በአፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ኦስትሪያ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ኦስትሪያ ቪየና አቀኑ።

በነገው እለት የሚካሄደው ፎረም በአዳዲስ ግኝቶችና ቴክኖሎጅ ልማት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይመክራል።

ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ በቆይታቸው በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጅን ለማስፋፋት እያከናወነች ያለውን ተግባር በተመለከተ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ከተለያዩ ሀገራት መሪዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ ኩባንያ ሀላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *