ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ አቀኑ።

ፕሬዚዳንቱ በቱርክ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በንግድ፣ ፣በኢንቨስትመንት እና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ነው የሚጠበቀው።

ቱርክ በበርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በኢትዮጵያ ከተሰማሩ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ መሆኗ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአሁን ወቅት ቱርክ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪን ጨምሮ በባቡር ግንባታ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች።

እስከ ፈረንጆቹ 2017 መጨረሻ ድረስ በኢትዮጵያ ከ150 በላይ የሚሆኑ የቱርክ ኩባንያዎች የተሰማሩ ሲሆን፥ 30 ሺህ ለሚጠጉ  ዜጎች የስራ እድል ፈጥረዋል።

እንዲሁም የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፈሰስ ማድረጋቸው ታውቋል።

ከዚህ በላፈ በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ከፍተኛ እንደሆነና በፍጥነት እያደገ የሚገኝ መሆኑን መረጃዎች ይጠቅማሉ።

ከዚህ በፊት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በፈረንጆቹ 2017 በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንት ኤርዶኸንም በ2015 በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

በኤፍሬም ምትኩ

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *