11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው

ትናንት የተጀመረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

የድርጅታዊ ጉባኤው በትናንትናው ዕለት በቀረበው የኢህአዴግ ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚጠቁመው ሪፖርት ዙሪያ ዛሬ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ተሳታፊዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ በቡድን በመሆን እየተወዩ ይገኛሉ።

ከሰዓት በኋላ ድርጅታዊ ጉባኤው በጋራ በቡድን ሪፖርቶች ላይ ይወያያል።

በጉባኤ በድምጽ ከሚሳተፉት 1 ሺህ ተሳታፊዎች መካከል 99 በመቶዎቹ መገኘታቸው ተመልክቷል።

በጉባኤው በርዕዮተ አለምም ሆነ በመስመር ጉዳይ ላይ የሚደረግ ውይይትም ሆነ የሚያዝ አጀንዳ እንደሌለ ተገልጿል።

banner ad

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *